World
ማላዊ ሚኒስትሮቿ በወር ከአንድ የሃገር ውስጥ ጉዞ በላይ እንዳያደርጉ ወስናለች።
ማላዊ ፥ ሚኒስትሮቿ በወር ከአንድ የሃገር ውስጥ ጉዞ በላይ እንዳያደርጉ ወስናለች።
የማላዊ ፕሬዚዳንት ፒተር ሙታሪካ በሚኒስትሮቻቸውና በምክትሎቻቸው የሚደረገው የሃገር ውስጥ ጉዞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መጨመሩ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።
በዚህም በወር ማድረግ የሚችሉት ጉዞ ከአንድ እንዳይበልጥ መገደባቸውን አስታውቀዋል።
ማላዊ በፋይናንስ ችግር በምፈተንበት ጊዜ ጉዞው አበልና ነዳጅን ጨምሮ ብዙ ወጪ እያስወጣኝ ነው ስትል ከአንድ በላይ ተጨማሪ ጉዞ ለማድረግ የፕሬዚዳንቱ ይሁንታ እንደሚያስፈልግም ገልፃለች።