Sports
ማንቸስተር ዩናይትድ ክሪስታል ፓላስን በማሸነፍ ደረጃውን ወደ 3ኛ ከፍ አደረገ
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 1 በማሸነፍ በሊጉ ያለውን ደረጃ ወደ 3ኛ ከፍ ማድረግ ችሏል።
የዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦችን ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፍፁም ቅጣት ምት እንዲሁም ቤንጃሚን ሼሽኮ በጨዋታ አስቆጥረዋል።
ክሪስታል ፓላስን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ያስቆጠረው ላክሮይክስ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
በሌላ ጨዋታ ፉልሃም ቶተንሃምን እንዲሁም ብራይተን ኖቲንግሃም ፎረስትን በተመሳሳይ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።