World
ሩሲያ ዋትስአፕን አገደች።
ሩሲያ ዋትስአፕን አገደች።
ከቀናት በፊት ቀስ በቀስ የሚተገበር እገዳ በቴሌግራም ላይ መጀመሯን የገለጸችው ሩሲያ ዋትስአፕ ህጌን ጥሷል በሚል ዛሬ ያገደች ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች ወደ መንግስታዊው የማክስ መተግበሪያ እንዲዞሩ ጠይቃለች።
የክሬምሊን ቃለ አቀባይ ዲምትሪ ፔስኮቭ ዋትስአፕ የሩሲያን ህግና እሴት ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆኑ መታገዱን ገልጸዋል።
ሩሲያ ባለፈው አመት አንዳንድ የስልክ ልውውጦችን በዋትስአፕ እና በቴሌግራም ማገዷ (https://t.me/tikvahethmagazine/25774) ሲታወስ ከባለፈው ታህሳስ ወር ጀምሮም ተጠቃሚዎች ዋትስአፕን በቪፒኤን እየተጠቀሙ መሆኑ ተነግሯል።
ዋትስአፕ እገዳውን ተከትሎ 100 ሚሊየን ሰዎችን ደህንነቱ ከተጠበቀ ግንኙነት መነጠል ኋላቀርነት ነው ብሏል።
ሩሲያ ለአመታት በፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስ ላይ እገዳ ያስቀመጠች ስትሆን ከወር በፊት የአፕሉን ፌስታይም ማገዷና ዩቲዩብ ላይም ገደብ መጣል መጀመሯ ተዘግቧል።
መረጃው የአልጄዚራ ነው።