Home News World
World

ስዊዘርላንድ የህዝብ ቁጥሯ ከ10 ሚሊየን እንዳይበልጥ ለመወሰን ህዝበ ውሳኔ ታደርጋለች።

February 13, 2026 4 weeks ago

ስዊዘርላንድ የህዝብ ቁጥሯ ከ10 ሚሊየን እንዳይበልጥ ለመወሰን ህዝበ ውሳኔ ታደርጋለች።

ስዊዘርላንድ በመጪው ሰኔ ወር የህዝብ ቁጥሯ ከ10 ሚሊየን እንዳይበልጥ ለመገደብ በቀረበው ሃሳብ ላይ ህዝበ ውሳኔ እንደምታደርግ ተገልጿል።

የቀረበው ሃሳብ የስዊዝ መንግስት አሁን ያለው የስዊዘርላንድ ህዝብ ቁጥር ከ9.1 ሚሊየን አልፎ 9.5 ሚሊየን ከደረሰ አዳዲስ ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ሰዎች እንዳይኖሩ እንዲያደርግ ኃላፊነት ይሰጣል።

በተጨማሪም የህዝብ ቁጥሩ 10 ሚሊየን ከደረሰና መቀነስ ካልጀመረ ሃገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት የነፃ የሰዎችና የእቃ እንቅስቃሴ እንድትወጣም ይደረጋል ይላል።

27 በመቶ ነዋሪዎቿ ዜጎቿ ያልሆኑት ስዊዘርላንድ ባለፈው አስር አመታት በዙሪያዋ ካሉት የአውሮፓ ሃገራት አንፃር የህዝብ ቁጥሯ በ5 እጥፍ ሲጨምር ይህም መሰረተ ልማት ላይ ጫና መፍጠሩንና የኪራይ ዋጋን መጨመሩ ተነግሯል።

መረጃው የዘ ጋርዲያን ነው።

Scroll to Top