World
በመጪው ቅዳሜ ምሽት 6 ፕላኔቶችን በአይናችን ማየት እንደምንችል ተገለጸ።
በመጪው ቅዳሜ ምሽት ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ኡራነስና ኔፕቲዩንን በአይናችን በሰማይ ላይ ማየት እንደምንችል ሲገለጽ ሁነቱ "Planetary Parade" ተብሎ እንደሚጠራ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሜርኩሪ፣ ቬነስ፣ ጁፒተር፣ ሳተርን፣ ኡራነስና ኔፕቲዩን ፀሐይ ከጠለቀች ወዲያውኑ የሚታዩ ሲሆን የእይታ ጊዜያቸውም ከ30 እስከ 45 ደቂቃ ይቆያል ተብሏል።
ይህ ክስተት የሚፈጠረው ፕላኔቶች በተመሳሳይ "Plane" ፀሐይን በሚዞሩበት ጊዜ ሲሆን ይህም የተለያዩ ፕላኔቶችን በተመሳሳይ አካባቢ በሰማይ ላይ እንድናይ ያስችላል።
ይታያሉ ተብለው ከሚጠበቁ ፕላኔቶች ውስጥ ኔፕቲዩን እና ኡራነስ በሙሉ ጨረቃ መኖርና በርቀት የተነሳ በአይናችን ለማየት እንደምንቸገር ሲነገር ሁለቱን ለማየት አጋዥ መሳሪያዎችን መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል ተብሏል።