Home News Sports
Sports

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታዎች

February 24, 2026 3 weeks ago

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ማጣሪያ ዛሬ አራት የመልስ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

ምሽት አምስት ሠዓት ላይ ኢንተር ሚላን ከቦዶ ግሊምት በሳን ሲሮ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው ዙር ባደረጉት ጨዋታ ቦዶ ግሊምት 3 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ኢንተር ሚላን ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከሁለት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ ይኖርበታል።

ተጋጣሚው ቦዶ ግሊምት ማሸነፍ፣ አቻ መውጣት እና በአንድ የግብ ልዩነት መሸነፍ 16ቱን መቀላቀል ያስችለዋል።

በሌላኛው መርሐ-ግብር ኒውካስትል ዩናይትድ ከካራባግ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ በሴይንት ጀምስ ፓርክ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በመጀመሪያው ጨዋታ 6 ለ 1 ያሸነፈው ኒውካስትል ዩናይትድ የማለፍ እድሉ እጅጉን ሰፊ ነው።

በአንጻሩ ተጋጣሚው ካራባግ በሂሳባዊ ስሌት ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት እድሉ በጣም የጠበበ ነው።

ባየር ሌቨርኩሰን ከኦሎምፒያኮስ ምሽት አምስት ሠዓት ላይ በቤይአሬና ስታዲየም ይጫወታሉ።

የጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰን በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ከሜዳው ውጪ 2 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው። ውጤቱንም ተከትሎ የማለፍ እድሉን አስፍቷል።

የግሪኩ ኦሎምፒያኮስ ወደ ጥሎ ማለፍ ለመግባት ከሁለት ጎል በላይ ልዩነት ማሸነፍ አለበት።

ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከክለብ ብሩዥ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ሳምንት ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ቡድን ጥሎ ማለፍ ይገባል።

Scroll to Top