Home News Business
Business

ንግድ ባንክ ከብድር 1% እና ከዲጂታል አገልግሎት 5% ለአደጋ ስጋት ፈንድ መሰብሰብ ጀመረ

February 23, 2026 3 weeks ago

በኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1386/2025 እና በደንብ ቁጥር 576/2025 ሁሉም ባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከሚሰጡት ብድርና ከዲጂታል ባንኪንግ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ  በደንቡ ላይ በተቀመጠው ስሌት መሰረት ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ በብሔራዊ ባንከ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ሂሳብ ገቢ እንዲያደርጉ ተደንግጓል፡፡

በመሆኑም ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባንካችን ከሚሰጠው ማንኛውም አይነት መደበኛ ብድር ላይ የሚለቀቀውን መጠን 1% (አንድ በመቶ)፣ እንዲሁም በሁሉም የባንካችን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች  ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5% (አምስት በመቶ) እየተጨመረ የሚሰበስብ እና ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ገቢ የሚያደርግ መሆኑን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡"ሲል ንግድ ባንክ አሳውቋል።

Scroll to Top