Home News World
World

ኢትዮጵያ በቱሪዝም ልማት ያሳየችው እድገት ለአፍሪካ ተምሳሌት መሆኑንየፓን አፍሪካ ቱሪዝም ቦርድ ፕሬዝዳንት ገለጹ

February 20, 2026 3 weeks ago

አምባሳደር ማርያም ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ ተፈጥሯዊና ባህላዊ ጸጋዎች በማድነቅ ኢትዮጵያ የሁላችንም ምድርና ቀደምት ሀገር ናት ብለዋል፡፡ኢትዮጵያውያን ጥንታዊ ባህልና ማንነታቸውን በመጠበቅ ለትውልድ ማስተላለፍ መቻላቸው እጅግ የሚያስደንቅ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የሚታዩ ውብ የባህል አልባሳት፣ ልዩ የቡና መዓዛና ሀገር በቀል ሙዚቃዎች ሀገሪቱ የራሷን ማንነት ጠብቃ እንድትቆይ ያደረገችው ጥረትና ሌሎችም ለዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ተመራጭ መዳረሻ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የሀገሪቱን የቱሪዝም እድገት ከሚያፋጥኑ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጥንካሬ በዋናነት አንስተዋል።

አየር መንገዱ ያለው ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ቱሪስቶች ያለምንም እንግልት ወደ ሀገሪቱ እንዲመጡና እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ንፁህ፣ ሰላማዊና የሕዝቧ እንግዳ ተቀባይነት የሚደነቅ መሆኑን የገለጹት ፕሬዝዳንቷ ይህ መልካም ባህሪ ቱሪስቶችን አንዴ መጥተው ሳይወሰኑ ደጋግመው እንዲመጡ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጸዋል።

አህጉሪቱ ያላትን እምቅ የቱሪዝም አቅም ለመጠቀም ትብብርና ድንበር የለሽ ፖሊሲ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው የአፍሪካ መሪዎች ለአፍሪካውያን የቪዛ ገደብን እንዲያነሱ ጥሪ አቅርበዋል።

Scroll to Top