World
ኢትዮጵያ ከተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች
ኢትዮጵያ ከተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች
ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት (SDSN) ትብብራቸውን ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሐደራ አበራ እና የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጄፍሪ ሳክስ ፈርመዋል።
በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና የተመድ የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናክር እንደሚረዳ መገለፁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
#Ethiopia #UN #Diplomacy