World
ኢትዮ ቴሌኮም እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲሱን ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል
የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን የአደጋ መከላከል አቅም በራስ አቅም ለመገንባት ባወጣው አዲስ ደንብ መሠረት፣ በቴሌኮም የድምፅና የዳታ አየር ሰዓት ሽያጭ ላይ የ5 በመቶ ክፍያ እንዲሰበሰብ መወሰኑ ይታወሳል።
ይህ ውሳኔ ከየካቲት ወር 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለቱም ኦፕሬተሮች በኩል ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።
ቁልፍ ነጥቦች
ተፈፃሚነት፦ በድምፅ (Voice) እና በዳታ (Data) አየር ሰዓት ግዢ ላይ 5 በመቶ ተቀናሽ ተደርጎ ለአገራዊ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ፈንድ ጽሕፈት ቤት ገቢ ይደረጋል።
ሕጋዊ መሠረት
በአዋጅ ቁጥር 1386/2017 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 576/2018 መሠረት።
ዓላማው
በተፈጥሮና ድንገተኛ አደጋዎች ወቅት በውጭ ዕርዳታ ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ፣ አገር በቀል የአደጋ መከላከያ አቅምን መገንባት።
ይህ ክፍያ በቴሌኮም ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ከባንኮች፣ ኢንሹራንስ፣ ነዳጅ፣ አየር መንገድ እና ሌሎች 17 የገቢ ምንጮች ላይ የሚሰበሰብ አገራዊ መርሃ ግብር አካል ነው።
የአየር ሰዓት ሲሞሉ ወይም የዳታ ጥቅል ሲገዙ የሚታይባችሁን የዋጋ ለውጥ በዚህ አውድ ተረዱት።