ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ሽፋንን ለማሳደግ ከዜድቲኢ ጋር የኔትወርክ ማስፋፊያ ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮ ቴሌኮም የኔትወርክ ማስፋፊያ እንዲሁም ማዘመኛ ስምምነት ከዜድቲኢ ኮርፖሬሽን ጋር ያጠናቀቀ ሲሆን ይህም አገሪቱ የዲጂታል መሠረተ ልማት ዝርጋታዋን እያፋጠነች ባለችበት ወቅት ከፍተኛ ፍጥነት ያለው ግንኙነትን ለማስፋት ያለመ ነውም ተብሏል።
ስምምነቱ የተፈረመው በባርሴሎና በተካሄደው የሞባይል ወርልድ ኮንግረስ 2026 ሲሆን የሁለቱ ኩባንያዎች ሥራ አስፈፃሚዎች በዓመታዊ የኢንዱስትሪ ስብሰባው ጎን ለጎን ስብሰባ ባደረጉበት ወቅት ነው። ስምምነቱ በተለይም ውስን ግንኙነት ላላቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያላቸው የሞባይል ብሮድባንድ አገልግሎቶችን በማራዘም የኔትወርክ አቅምን ለማሳደግ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የተነደፈ ሲሆን የገጠር ቦታዎችም ከታቀዱት ውስጥ አንድ አምስተኛውን ያህል ይይዛሉም ተብሏል።
በስምምነቱ መሠረትም ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ በዜድቲኢ የሥራ አካባቢ 647 የኔትወርክ ጣቢያዎችን የሚሸፍን ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 115 አዳዲስ የገጠር አካባቢዎች ይገኙበታልም ተብሏል። ፕሮግራሙ ከተጠናቀቀም በኋላ የአራተኛ ትውልድ የሞባይል ህዝብ ሽፋንን ወደ 95.5 በመቶ እንደሚያሳድግ ይጠበቃል ሲል ኢትዮ ቴሌኮም ገልጿል።
ይህ ስምምነት የመጣውም የኢትዮጵያ ኦፕሬተር አስተዳደር ከቻይና አቻው ቡድን ዋና መሥሪያ ቤት እና ክልል ቡድኖች መካከል ድርድር ከተደረገ በኋላ እንደሆነም ተገልጿል።
ኩባንያዎቹ ከባህላዊ የቴሌኮም አቅርቦቶች ባሻገርም የዲጂታል መሠረተ ልማት እና አገልግሎቶችን በማስፋፋት ላይ ያተኮረው “Next Horizon: Digital & Beyond 2028” በመባል ከሚታወቀው የኢትዮ ቴሌኮም የረጅም ጊዜ የኮርፖሬት ስትራቴጂ ጋር በተያያዘም ተወያይተዋል።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ አዳዲስ ተጫዋቾች ቢገቡም ከ70 ሚሊዮን በላይ ተመዝጋቢዎችን በማገልገል እንዲሁም እየጨመረ የመጣውን የሞባይል ዳታ ፍላጎት ለማሟላት በኔትወርክ መስፋፋት ላይ ከፍተኛ ኢንቨስት በማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም በአገሪቱ ውስጥ ትልቁ ኦፕሬተር ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።
እንደ ዜድቲኢ እና ኤሪክሰን ካሉ ዓለም አቀፍ የመሳሪያ አቅራቢዎች ጋር ያለው ሽርክና ኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማትን ለማሻሻል እና ዲጂታል መዳረሻን በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ በምትገኘው ሀገር ለማስፋፋት የምታደርገውን ሰፊ ጥረት አካል ነው።