Home News Business
Business

ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱ 53 የአፍሪካ ሃገራት ወደ ቻይና የሚልኩት ምርት ላይ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ታሪፍ እንደማይኖር ቻይና አስታውቃለች።

February 15, 2026 4 weeks ago

ከቻይና ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመሰረቱ 53 የአፍሪካ ሃገራት ወደ ቻይና የሚልኩት ምርት ላይ ከመጪው ግንቦት ወር ጀምሮ ታሪፍ እንደማይኖር ቻይና አስታውቃለች።

ኢትዮጵያ ከዚህ ፖሊሲ ቀድማ ተጠቃሚ የነበረች ስትሆን የአሁኑ ዜና በፊት በ33 ሀገራት ተወስኖ የነበረውን የተጠቃሚ ሀገራት ቁጥር ወደ 53 ከፍ ማለቱ ነው።

በኢትዮጵያ እና ቻይና መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በ2025 ብቻ 13 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። 

ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ብቻ ወደ ቻይና 34 ሺ ሜትሪክ ቶን ቡና የላከች ሲሆን ከዚህም ከ218 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝታለች። 

ቻይና የኢትዮጵያ የቡና ገበያ ውስጥ 5ኛዋ ቀዳሚዐመዳረሻ መሆን ስትችል ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታት 7ኛ መዳረሻ ነበረች።

በ2025 በአፍሪካና ቻይና መካከል ፦

የንግዱ መጠን 2024 ከነበረበት በ17.7% ጨምሯል።

ቻይና ወደ አፍሪካ የላከቸው ምርት 225 ቢሊየን ዶላር ነው።

አፍሪካ ወደ ቻይና የላከችው ደግሞ 123 ቢሊየን ዶላር ነበር።

Scroll to Top