Home News World
World

ከፀሐይ ኃይል 1 ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጩ አራት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

February 16, 2026 4 weeks ago

በሶማሌ ክልል 1 ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው አራት የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች ከ9 ሺ 500 በላይ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ አስችሏል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ገልጿል።

በአሁን ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ 38 የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሲሆን በሶማሌ ክልል ብቻ 8 የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

Scroll to Top