Home News Business
Business

የማዕድን ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የፖታሽ ምርት ፈቃድ ሰጠ።

March 14, 2026 21 hours ago

የማዕድን ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የፖታሽ ምርት ፈቃድ ሰጠ።

የፖታሽ ፕሮጀክቱ በሐምሌ 2025 በንግድ ደረጃ የማዕድን ማውጣት ፈቃድ ለማግኘት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የቀረበለትን ማመልከቻ ተከትሎ እንደሆነ ተዘግቧል። ኩባንያውም በአፋር ክልል በዳሉል ወረዳ 365 ካሬ ኪሎ ሜትር የፖታሽ ክምችት የማግኘት መብት እንዳለውም ተነግሯል።

የፖታሽ ፕሮጀክቱ መንግስት የኢንዱስትሪ ምርትን ለማስፋፋት እና ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር ከሚደረገው ጥረት አካል ሆኖ ከሚደግፋቸው የማዕድን ተነሳሽነቶች አንዱ ሲሆን የሚኒስትሮች ምክር ቤትም በጥር ወር ባካሄደው አምስተኛው መደበኛ ስብሰባ ከማዳበሪያ እና ከፖታሽ ምርት ፈቃዶች ጋር የተያያዙ ረቂቅ ስምምነቶችን ገምግሞ ለቀጣይ ማጽደቂያዎች መሠረት ጥሏልም ተብሏል። ሚኒስቴሩም የምርት ፈቃዱ የቁጥጥር መስፈርቶችን እና መደበኛ የማፅደቂያ ሂደቶችን ተከትሎ ለኩባንያው ቀጣዩን የልማት ምዕራፍ እንዲጀምር መንገድ እንደሚጠርግ አክልዋል።

ፈቃዱ ከሌሎች ሁለት የማዕድን ኩባንያዎች ጋር የተጠናቀቁ ስምምነቶች አካል ሲሆን እነዚህ ስምምነቶችም ለ ZY TB-DAIM Steel Manufacturing የብረት ማዕድን ምርት ፈቃድ እንዲሁም ለ ቤሮ ማይኒንግ እና ትሬዲንግ የወርቅ ምርት ፈቃድ መስጠት ናቸው። በዚህ ስምምነትም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከ 4.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ኢንቨስት እንዳደረገም ተነግሯል።

EIH እንደ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም ያሉ ዋና ዋና አካላትን ጨምሮ ከ40 በላይ የመንግስት ባለቤትነት ያላቸውን ድርጅቶች የሚያስተዳድር ሲሆን ፖርትፎሊዮውም ወደ 250,000 የሚጠጉ ሰዎችን በመቅጠር ለአገር አቀፍ ምርት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይም ይገኛል።

Scroll to Top