Home News World
World

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ 10% ገደማ ጭማሪ አሳየ

March 2, 2026 2 weeks ago

ለኢትዮጵያ ነዳጅ ግዥ ዋነኛ መለኪያ የሆነው የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ የ9.58 በመቶ ወይም የ6.82 ዶላር ጭማሪ በማሳየት በበርሜል 79.85 ዶላር ደርሷል።

ይህ ጭማሪ ይህም ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ትልቁ የአንድ ቀን የዋጋ ጭማሪ ሆኖ ተመዝግቧል።

በመካከለኛው ምስራቅ በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በኢራን መካከል የተከሰተው ወታደራዊ ግጭት ወደ ከፋ ደረጃ መሸጋገሩ እና የፋርስ ባሕረ ሰላጤ የነዳጅ ማጣሪያዎች ምርት ለዓለም ገበያ እንዳይቀርብ እንቅፋት ይፈጠራል የሚለው ስጋት ለዚህ ድንገተኛ መናር ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።

የዓለም የነዳጅ አቅርቦት 20 በመቶ ገደማ በዚሁ የሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፍ ሲሆን 10 በመቶ የሚጠጋው የዋጋ ጭማሪ ዛሬ ሰኞ የታየው ቅዳሜና እሁድ የዓለም የንግድ ማዕከላት ዝግ በመሆናቸውና ዛሬ ገበያው ገና እንደተከፈተ በመሆኑ ነው።

ተንታኞች በመካከለኛው ምሥራቅ የተነሳው ጦርነት የማይረግብ ከሆነ የነዳጅ ዋጋ እስከ 100 ዶላር ሊያሻቅብ እንደሚችል እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

Scroll to Top