Technology
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት የሚወስዱ ተማሪዎች ቁጥር በ3 ዓመት በእጥፍ ቀንሷል ተባለ።
በኢትዮጵያ ላለፉት ሦስት ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና (TVET) የተመዝጋቢ ተማሪዎች ቁጥር ከ50 በመቶ በላይ ቀንሷል ተብሏል።
የአገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ጥናት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በ2013 የትምህርት ዘመን 478 ሺህ 910 የነበረው የሰልጣኞች ቁጥር ወደ 213 ሺህ 663 ዝቅ ብሏል።
በምክንያትነት ከተጠቀሱት ጉዳዮች መካከል
ቀደም ሲል የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ተማሪዎችን ሲቀበሉ የነበረው ከ10ኛ ክፍል ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ግን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲቀበሉ መደረጉ ጊዜያዊ ክፍተት መፍጠሩ ተጠቅሷል።
በክፍል ውስጥ የሚሰጠው ሥልጠና በአሰሪዎች ዘንድ ካለው ዘመናዊ የሥራ ፍላጎት ጋር አለመጣጣሙ
አሰልጣኞች በኢንዱስትሪው ውስጥ በቂ ልምድ ማጣታቸው፣ የመሰረተ ልማት እጥረት እና የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አናሳ መሆን በዘርፉ ላይ እንቅፋት ሆነዋል ተብሏል።
ዘገባው የካፒታል ነው።