Home News Business
Business

የነዳጅ ኩባንያዎች የገበያ ድርሻ በአዲስ መመሪያ ሊወሰን ነው

March 1, 2026 2 weeks ago

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የኩባንያዎችን የገበያ ድርሻ በአዲስ አሰራር ለመወሰን ማቀዱን አስታውቋል።

እስካሁን የነበረው ስርዓት ኩባንያዎች ከጅቡቲ የሚጭኑትን ነዳጅ በራሳቸው ፍላጎት እንዲስሩ ያስችል በመሆኑ ህገ-ወጥነትና ፍትሃዊ ያልሆነ ስርጭት እንዲፈጠር አድርጓል። በተለይም ለራሳቸው ማደያዎች ቅድሚያ መስጠታቸው የአቅርቦት መስተጓጎል እንደፈጠረ ተገልጿል።

አዲሱ መመሪያ የገበያ ድርሻን 40% በማደያ ብዛት፣ 40% በመቅጃ ማሽን ቁጥር እና 20% በታንከር የመያዝ አቅም ላይ በመመስረት እንዲደለድል ይደነግጋል።

በተጨማሪም ለልማት ፕሮጀክቶች የሚሰጥ ነዳጅ በቀጥታ እንዲቀርብ እና ከየኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ጋር የአንድ ወር የጭነት ፕሮግራም በጋራ እንዲዘጋጅ ተወስኗል።

አዲሱ አሰራር ተግባራዊ ሲሆን የአቅርቦት መስተጓጎል መቀነስ እና በጅቡቲ የቦቴዎች መጨናነቅ መቆም እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

Scroll to Top