World
የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የ2026 የሕብረቱን መሪ ሀሳብ አጽድቋል
ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል።
ጉባኤው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ባደረገው 48ኛ መደበኛ ስብሰባ በአጀንዳነት ያቀረበውን የ2026ቱን የሕብረቱ መሪ ሀሳብ አጽድቋል።
መሪ ሀሳቡ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚል ነው።
የአፍሪካ ሕብረት 2026ን የውሃ ዓመት ሲልም ሰይሞታል።
ህብረቱ መሪ ሀሳቡን ይፋ ማድረጊያ መርሐ-ግብር ዛሬ ከቀትር በኋላ አካሄዷል።
በዚም መሪ ሀሳቡን መሰረት ያደረጉ ስራዎች እ.አ.አ በ2026 ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ይከናወናሉ።