World
የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ደረሰኝ ያላሳተሙና ያልተረከቡ ግብር ከፋዮች በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ማሳወቅ እንዳለባቸው ጥሪ አቀረበ።
የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ደረሰኝ ያላሳተሙና ያልተረከቡ ግብር ከፋዮች በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ማሳወቅ እንዳለባቸው ጥሪ አቀረበ።
ጽሕፈት ቤቱ ባወጣው መመሪያ መሠረት፣ ከታኅሣሥ 1/2017 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም ግብር ከፋዮች በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የታተመ ደረሰኝ እንዲጠቀሙ መወሰኑ ይታወቃል።
ሆኖም ግን በርካታ ድርጅቶች እስካሁን ድረስ የደረሰኝ ሕትመት ጥያቄ እንዳላቀረቡና የታተሙ ደረሰኞችንም እንዳልተረከቡ ታውቋል።
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የቀረቡለትን የሕትመት ትዕዛዞች በሙሉ አጠናቆ ማቅረቡን ገልጿል።
ይህን ተከትሎ ከታኅሣሥ 1 ቀን 2017 ዓ.ም. እስከ ታኅሣሥ 30፤ 2018 ዓ.ም. ድረስ የደረሰኝ ሕትመት ጥያቄ አቅርባችሁ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ያልተረከቡ::
እንዲሁም እስካሁን ጥያቄ ያላቀረቡ ግብር ከፋዮች ይህ ማሳሰቢያ ከወጣበት ቀን ከየካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሪፖርት እንድታደርጉ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።