World
የዓድዋ ድል ለጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግል ፋና ወጊ ነው!! ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ!
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ለመውጣት ለሚያደርጉት ትግል ብርታትን የሰጠና የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ እርሾ መሆኑን ገልጸዋል።
ጥቁር ሕዝቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጠንካራ ኢኮኖሚ መገንባትና በሕብረት መቆም እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ዓለም አቀፉ የጥቁር ሕዝቦች ማዕከል የ2026 ዓመታዊ የምክር ቤት ጉባኤውን በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እያካሄደ በሚገኘው መድረክ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ።