ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
እንኳን ለ130ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ።
የዐድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን የማይቀየር ዐቋምና ዐቅም ያሳየ ድል ነው። ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ብሔራዊ ጥቅም፣ ነጻነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይቀየር ዐቋም አላቸው።
ይሄንን ዐቋማቸውን በጽኑ መሠረት ላይ ለመትከል ደግሞ ሁሉንም አቅማቸውን ይጠቀማሉ።
ሥርዓታትና መሪዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፤ በአንዳንድ ጉዳዮች ልዩነቶች ይኖሯቸው ይሆናል ስለ ሀገራቸው ያላቸው ዐቋምና ለሀገራቸው የሚያወጡት አቆም ግን አይቀየርም።
በዚያ ጊዜ ሀገራቸውን ከድተው ከጠላት ጋር ያበሩ ባንዳዎች ነበሩ። ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ ዘላቂ የሀገራቸውን ጥቅም የሸጡ ምንደኞችም ነበሩ። ከባዳ ጋር ወግነው ወገናቸውን ያስማሙ ደላሎችም ነበሩ።
ጀግኖች እናቶቻችን እና አባቶቻችን የተዋጉት ከወራሪው የጣሊያን ጦር ጋር ብቻ አልነበረም።
የዐድዋ ድል በዓል እነዚህን ሁሉ የምናስታውስበት ነው። የዐድዋ ድል በዓል የኢትዮጵያውያንን ዐቅምና አቋም እንደገለጠው ሁሉ ዛሬም በጸና አቋም፣ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዐቅም የምንገልጥበት ጊዜ ነው።
በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን እና በዲጂታል ሀገራችን ያላትን ዐቅም መግለጥ አለብን። የዐድዋን ድል በሁሉም ዘርፍ ለመድገም የኢትዮጵያ ዐቅም ጽኑ መሠረት ሊኖረው ይገባል።
ሀገርን ዐቅም ያሳድጋታል ዐቅም ይገነባታል። ሀገርን ዐቅም ይሠራታል ዐቋም ያጸናታል። ሀገርን ዐቅም ያራምዳታል፤ ዐቋም ያሻግራታል።
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!